ቶጎ የጤና መድኅን አገልግሎቷን በግላቸው ወደ ሚሰሩ ሠራተኞች በማስፋፋት በአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች
17:28 25.10.2025 (የተሻሻለ: 17:34 25.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቶጎ የጤና መድኅን አገልግሎቷን በግላቸው ወደ ሚሰሩ ሠራተኞች በማስፋፋት በአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች
የእደ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ነጋዴዎች እና ገበሬዎች አሁን ላይ በሁሉን አቀፉ የጤና መድኅን መርሃ ግብር ተቀላቅለው ተጠቃሚዎች መሆን ችለዋል።
ሠራተኞች በተለያዩ የክፍያ አማራጮች ለመርሃ ግብሩ መዋጮ ማድረግ ይችላሉ፤ በወር 18 ዶላር፣ በሩብ ዓመት 50 ዶላር፣ በግማሽ ዓመት 96 ዶላር ወይም በዓመት 181 ዶላር ይጠበቅባቸዋል።
መርሃ ግብሩ በቅርቡ የትዳር አጋራቸው ለሞቱባቸው አባወራ/እማወራ እንዲሁም ለወላጅ አልባ ሕጻናት ተደራሽ ሆኗል።
የብሔራዊ ማኅበራዊ ዋስትና ፈንድ በቀጣይ ወራት መርሃ ግብሩን ወደ ሌሎች የሙያ ዘርፎች ለማስፋት አቅዷል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X