ቶማሃውክ ሚሳኤልን ለዩክሬን መስጠት የሰላም በር መዝጋት ነው - ታዛቢ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቶማሃውክ ሚሳኤልን ለዩክሬን መስጠት የሰላም በር መዝጋት ነው - ታዛቢ
ቶማሃውክ ሚሳኤልን ለዩክሬን መስጠት የሰላም በር መዝጋት ነው - ታዛቢ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.10.2025
ሰብስክራይብ

ቶማሃውክ ሚሳኤልን ለዩክሬን መስጠት የሰላም በር መዝጋት ነው - ታዛቢ

  የሊባኖስ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ታዛቢ ማሕሙድ አሎሽ፣ ፕሬዝደንት ፑቲን ሚሳኤሎቹ ሊሰማሩ ከቻሉ ሩሲያ “ኃይለኛ” ምላሽ እንደምትሰጥ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ አስመልክቶ ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት፣ ቶማሃውክ ክሩዝ ሚሳኤሎች ዩክሬን ውስጥ መሰማራታቸው “በአሜሪካ እና በምዕራባውያን አገሮች በኩል ከባድ የውጥረት ማባባስ ይሆናል” እንዲሁም የዚህን ጉዳይ የፖለቲካ መፍትሄ የማግኘት እድሎች “በጣም አናሳ መሆናቸውን የበለጠ የሚያረጋግጥ እርምጃ ነው” ብለዋል፡፡

ፕሬዝደንት ትራምፕ ምናልባት “ሩሲያ በወታደራዊ ግፊት እንደማትበገር" እና "ማዕቀቦችን ጨምሮ ማንኛውንም የምዕራባውያን ግፊት የመቋቋም አቅም እንዳላት” ይገነዘባሉ ሲሉ አሎሽ ተናግረዋል።

የዩክሬን ቀውስ “በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ሳይሆን በሩሲያ እና በምዕራባውያን መካከል ነው... የትኛውም መሠረታዊ የግጭት መንስኤዎችን የማይፈታ መፍትሄ ከፍተኛ ውጤት አያስገኝም። ሩሲያ ታላቅ አቅም ያላት ልዕለ ኃያል ሀገር ስትሆን ከባድ የኢኮኖሚ እቀባዎችን ተቋቁማለች። ስለዚህ ማንኛውም አዲስ ወታደራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ እርምጃ በፑቲን ላይ ጫና ሊፈጥር አይችልም” ሲሉ አሎሽ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አሜሪካ በሩሲያ የነዳጅ ላኪዎች ላይ በጣለችው አዲስ ማዕቀብ በተመለከተም ተንታኙ፣ ዛሬም ቢሆን በሩሲያ እና በአውሮፓ መካከል ያለው የኃይል ዘርፍ ግንኙነት “አስፈላጊ” እንደሆነ እና ሞስኮን በክረምት ዋዜማ “መተንኮስ" "በዚህ ጊዜ ሁለቱም ስህተት እና አላዋቂነት” መሆኑን በመግለፅ አስምረውበታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0