ኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትና የግብፅን የጋራ መግለጫ “ችግር ያለበት” እና “በእጅጉ የሚያበሳጭ” ስትል አወገዘች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትና የግብፅን የጋራ መግለጫ “ችግር ያለበት” እና “በእጅጉ የሚያበሳጭ” ስትል አወገዘች
ኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትና የግብፅን የጋራ መግለጫ “ችግር ያለበት” እና “በእጅጉ የሚያበሳጭ” ስትል አወገዘች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትና የግብፅን የጋራ መግለጫ “ችግር ያለበት” እና “በእጅጉ የሚያበሳጭ” ስትል አወገዘች

በብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመግለጫው፣ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም በሁለቱ ወገኖች የወጣው "የጋራ መግለጫ" ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ያላትን የቅኝ ግዛትና የብቸኝነት የይገባኛል ጥያቄ የሚያስተጋባ እንዲሁም የሌሎች ተፋሰሱን አገሮችን አመለካከትና ጥቅም ሙሉ በሙሉ ያገለለ መሆኑን እንደሚያሳይ ገልጿል።

"የዓባይ ወንዝ አስራ አንድ ተፋሰስ አገራት እንዳሉት ማስታወስ ያስፈልጋል። መግለጫው ይህንን እውነታ ችላ ያለ እና በእነዚህ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የሚኖሩ ወደ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መብቶች፣ ፍላጎት እና ኅልውና የካደ ነው" ሲል ኤምባሲው በመግለጫ አሳስቧል።

መግለጫው አክሎም “የአውሮፓ ሕብረት ከግብፅ ጋር በሁለትዮሽ መድረክ ኢትዮጵያን ለማዳከም መወሰኑ የሚያስፀፅት ነው” ብሎታል፡፡

“ ‘የጋራ መግለጫው’ ኢትዮጵያ እና አውሮፓ የነበራቸውን ታሪካዊ ግንኙነት ጥራት የሚጻረር ትክክለኛ ያልሆነ፣ የተዛባና ጠላትነት የተሞላበት አቋም ያሰራጨ ነው፡፡” ብሏል።

የአውሮፓ አኅጉር በርካታ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሃብቶችና የውሃ ተፋሰስ አቀፍ የትብብር ስልቶች እንዳሉት ከግምት ውስጥ ሲገባ፣ የአውሮፓ ሕብረት ዓለም አቀፍ ሕግን በተዛባ መንገድ መመልከቱ በጣም አሳዛኝ መሆኑን ዓለም አቀፍ ህኝ ጠቅሶ አጽንኦት ሰጥቷል።

በብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ኢትዮጵያ በ"ጋራ መግለጫው" ላይ የተንፀባረቁትን እጅግ የተሳሳቱ እና ተገቢ ያልሆኑ አቋሞችን ለማረም ከአውሮፓ ሕብረት እና አባል ሀገራቱ ጋር እንደምትነጋገር አስታውቋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0