ሀገር በቀል እውቀት የሥነ ልኬታችን መሣሪያ ነው - የዘርፉ ተመራማሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሀገር በቀል እውቀት የሥነ ልኬታችን መሣሪያ ነው - የዘርፉ ተመራማሪ
ሀገር በቀል እውቀት የሥነ ልኬታችን መሣሪያ ነው - የዘርፉ ተመራማሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.10.2025
ሰብስክራይብ

ሀገር በቀል እውቀት የሥነ ልኬታችን መሣሪያ ነው - የዘርፉ ተመራማሪ

ሀገር በቀል እውቀት ሀገራት ያላቸው እሴት የሚለካበት ዋንኛ መሣሪያ ነው ሲሉ የዘርፉ ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያው አብዱልፈታህ አብደላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"የማንነታችን መለኪያ ነው፤ መለኪያህ ካንተ ወጣ ማለት በሌሎች መለኪያ ውስጥ ትገባለህ።  የሌሎች መለኪያ ደግሞ ሁልጊዜ ላንተ ጥሩ ላይሆን ይችላል" ሲሉ የምዕራቡ ዓለም በልኬቱ ልክ ይዞት የመጣውን ስሁት የፆታ ብያኔን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

የሀገር በቀል እውቀት ተመራማሪው፣ በሌላ በኩል አፍሪካ ባለፉት ዘመናት በሌሎች አካላት አሁን ላይ ደግሞ እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) በመሳሰሉ ድርጅቶች ለሚደረግ ድጋፍ ቅደመ ሁኔታዋች ተቀምጠውላታል ሲሉ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል።

“መንግሥታት ድጋፍ የሚያገኙት ከውጭ ነው፡፡ ያ ዳረጎት ደግሞ ከፍተኛ ነው፡፡ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛቶች በመንግሥቶቻችን ላይ ቀላል እንዳይመስልህ፡፡ ... መንግሥቶቻችን በነጻ ፍላጎታቸው፣ በነጻ ምኞታቸው ይሰራሉ ወይ? የቅኝ ግዛት ስርዓቱ አብቅቷል ወይ? ምሁሩ ይሄንን ነው መመለስ ያለበት፡፡ ይሄንን ነው ሁላችንም መገንዘብ ያለብን፡፡” ሲሉ አብዱልፈታህ አብደላ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0