የተባበሩት መንግሥታት 1945 አስተሳሰቡ መውጣት አለበት ሲሉ የካሜሩን የፖለቲካ ፈላስፋ ገለጹ

ሰብስክራይብ

የተባበሩት መንግሥታት 1945 አስተሳሰቡ መውጣት አለበት ሲሉ የካሜሩን የፖለቲካ ፈላስፋ ገለጹ

የካሜሩን የፖለቲካ ፈላስፋ እና የኬፐር "ቲንክታንክ" መሥራች ያንብ ንቲምባ እንደተናገሩት፤ የተባበሩት መንግሥታት የተወለደው ከጦርነት ፍርስራሾች በመሆኑ፣ ከ80 ዓመታት በኋላም በተመሳሳይ የጦርነት አስተሳሰብ እየተመራ ይገኛል።

በትናትናው ዕለት በተከበረው የተባበሩት መንግሥታት ቀን ለስፑትኒክ አፍሪካ ሲናገሩ፤ “ዓለምን በጦርነት ጊዜ በተፈጠረ ድርጅት ማደራጀት እና መግዛት መቀጠል አንችልም። በሰላም ጊዜ የሚነሳ አዲስ ድርጅት መፍጠር አለብን” ብለዋል።

ፈላስፋው እውነተኛ ዓለም አቀፍ ነፃነትን እና እኩልነትን የሚያግድውን እና በተመድ ሥርዓት ውስጥ የቀጠለውን “የቅኝ ግዛት ተገዳሮቶች” ነቅፈዋል።

ሩሲያ እና ሌሎች ሀገራት አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ጠንካራ ድምጽ እንዲኖራት የምታቀርበውን ጥያቄ በመደገፍ ያደረጉትን ጥረት አሞግሰዋል። “አብዛኞቹ የአፍሪካ ምሁራን ወይም ፖለቲከኞች ሩሲያ እና ሌሎች በዓለም ዙሪያ ያሉ አንዳንድ ሀገራት አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ በሚጠይቁት ጥረት የሚያደርጉትን ነገር ያደንቃሉ” ብለዋል። ሆኖም ችግሩ ከዚያ የጠለቀ መሆኑን ንቲምባ ይገልፃሉ፡፡

“አፍሪካ ሀገር አይደለችም፤ አፍሪካ አኅጉር ናት... የአውሮፓ ወይም የምዕራባውያን ሀገሮች የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ቀደም ሲል እንደተነጋገርነው፤ በተመድ ውስጥ የምንሰማው እና የምንገነዘበው ‘የቅኝ ግዛት መንፈስ’ ነው። አሁንም ያ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ፣ የአሠራር ዘይቤ አላቸው። አፍሪካ በተመድ ውስጥ የተወሰነ ደረጃ ያለው ተሳትፎ እንዳይኖራት የሚከለክሉትም ለዚህ ነው” ብለዋል።

ንቲምባ ሲያጠቃልሉም፤ የዛሬው ፈተና የተባበሩት መንግሥታትን ማሻሻል ሳይሆን ባለብዙ ዋልታ እና ከቅኝ ግዛት በኋላ ያለውን የዓለም እውነታዎች እና ፍላጎቶች በሚያንፀባርቅ መልኩ ሙሉ በሙሉ ማዋቀር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0