ኮት ዲቯር የፕሬዝዳንታዊ ምርጫዋን ዛሬ እያካሄደች ትገኛለች
14:33 25.10.2025 (የተሻሻለ: 14:34 25.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኮት ዲቯር የፕሬዝዳንታዊ ምርጫዋን ዛሬ እያካሄደች ትገኛለች
ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጉ የኮት ዲቯር ዜጎች ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድምጻቸውን ይሰጣሉ።
በሥልጣን ላይ የሚገኙት የ83 ዓመቱ ፕሬዝዳንት አላሳኔ ኦታራ ለአራተኛ ጊዜ ለመመረጥ እየተወዳደሩ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ዙር ያሸንፋሉ ተብሎ በሰፊው ይጠበቃል።
አራት እጩዎች ኦታራ እየተፎካከሩ ነው፦
የቀድሞ የንግድ ሚኒስትር፣ ነጋዴ እና የፓርላማ አባል የ60 ዓመቱ ዣን ሉዊ ቢሎን በዲሞክራቲክ ኮንግረስ ስር።
የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት የ76 ዓመቷ ሲሞን ኤይቬት ግባግቦ "ኬፔብል ጀኔሪሽን ሙቭመንት" ወክለው።
የ69 ዓመቱ አሁዋ ዶን ሜሎ፤ የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው መሃንዲስና ፖለቲከኛ ሲሆኑ በግል እጩነት።
የ69 ዓመቱ ሄንሪየት ላጉ በብሔራዊ እርቅ፣ በፖለቲካዊ ውይይት እና በተቋማዊ መረጋጋት የሚያምኑት የፖለቲካ አጋሮች ለሰላም ጥምረት ወክለው እየተወዳደሩ ነው።
ምርጫውን ለመከታተል ከአይቮሪ ኮስት የሲቪል ማኅበራት የተውጣጡ አንድ ሺህ የሚጠጉ ታዛቢዎች እንዲሁም ከኢኮዋስ እና ከአፍሪካ ሕብረት የተላኩ 251 ተወካዮች ተሰማርተዋል።
የምርጫው ውጤት በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X