በሩሲያ ላይ የተጣለው የነዳጅ ማዕቀብ አሜሪካ ከእውነታው ምን ያህል እንደራቀች ያሳያል
በሩሲያ ላይ የተጣለው የነዳጅ ማዕቀብ አሜሪካ ከእውነታው ምን ያህል እንደራቀች ያሳያል
አንጋፋው የፖለቲካ ተንታኝ ግሬግ ሳይመንስ አሜሪካ በሩሲያ ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ተከትሎ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ያለበትን ሁኔታ አስመልክቶ ለስፑትኒክ ሲናገሩ፣ "ወሳኝ የሆኑ እንደ ኃይል እና ነዳጅ ያሉ አቅርቦቶችን ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መገደብ ዋጋው እንዲጨምር ያደርገዋል። ይህ መሠረታዊ ኢኮኖሚክስ ነው" ብለዋል።
ሳይመንስ እንዳሉት አሜሪካ በ"ኢኮኖሚያዊ ጦርነት"ላይ ያላት "ልክፍት" እና ሩሲያን በኃይል ማስገደድ ይቻላል የሚለው አስተሳሰብ ከእውነታው ጋር አይጣጣምም።
የዳፍዶል ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነት ፕሮፌሰሩ አጽንዖት ሰጥተው ሲናገሩ፤ "በርዕዮተ ዓለም ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ እና በውስጡ የያዘው የአዳኝነት ስሜት አለ፤ ነገር ግን ሊገመቱ የሚችሉትን ውጤቶች እና ተፅዕኖዎች በተመለከተ ፍጹም ቸልተኝነት ይታያል።"
ሳይመንስ አክለውም፥ "አሜሪካ እ.ኤ.አ.በ1991 ሶቪዬት ሕብረት ከፈረሰች በኋላ የተፈጠረች ተገዳዳሪ የሌላት፣ ፍፁም የበላይ አካል እንደሆነች ማሰብ እና ማመንን አሁንም የምትቀጥል ትመስላለች።ይህ ከእንግዲህ እውነት አይደለም"። አሜሪካ "ከባድ ችግር" ውስጥ ሳለችም፥ ትክክለኛ የቁሳቁስ አቅሟን መሠረት ባደረገ መልኩ ምኞቷን መግታት አልቻለችም።
ወደ ንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ጦርነት ሲመጣ "አሜሪካ ሩሲያን የምትፈልገው ሩሲያ አሜሪካን ከምትፈልገው በላይ ነው" ያሉት ሳይመንስ፤ ሁኔታዎች ከከረሩ ዋሽንግተን ኢኮኖሚዋ እንዲቀጥል የሚያስፈልጋትን "ወሳኝ አቅርቦቶች" ልታጣ እንደምትችል አስምረውበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X