የማጣሪያ ፋብሪካ ፍንዳታዎች ሃንጋሪ እና ሮማኒያ ከሩሲያ ጋር ላላቸው ግንኙነት ኔቶ የጣለባቸውን ቅጣት ያሳያል
21:08 24.10.2025 (የተሻሻለ: 21:14 24.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማጣሪያ ፋብሪካ ፍንዳታዎች ሃንጋሪ እና ሮማኒያ ከሩሲያ ጋር ላላቸው ግንኙነት ኔቶ የጣለባቸውን ቅጣት ያሳያል
የጂኦፖለቲካል ተንታኝ የሆኑት ኮሜ ካርፔንቲየር ዴ ጉርደን፣ በሃንጋሪ እና ሮማኒያ በሚገኙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ላይ በቅርቡ ስለደረሱት ፍንዳታዎች ለስፑትኒክ ሲናገሩ፤ “በተለያዩ የአውሮፓ ክፍሎች ውስጥ በጣም ንቁ የሆነ የዩክሬን የጥፋት መረብ አለ” ብለዋል።
🟠 ፍንዳታዎቹ አውሮፓ በኔቶ የሚራገበውን የአሜሪካን አጀንዳ እየፈፀመች በመሆኑ የሃንጋሪን እና የሮማኒያን “ከሩሲያ ጋር ያለውን የኃይል ግንኙነት” ለማስቆም የተደረገ የአውሮፓ “ሆን ተብሎ የተፈፀመ የማፍረስ ተግባር” አካል ሊሆኑ እንደሚችሉ አልገለጹም።
🟠 ተንታኙ ምዕራባውያን የስትራቴጂክ ዓላማዎቻቸውን በሕገወጥ መንገድ እንዲያሳኩ የሚረዳ “ሰፋ ያለ አጀንዳ” ሊኖራቸው እንደሚችል ጠቁመዋል።
ጉርዶን አጽንዖት ሰጥተው ሲናገሩ፣ “ዓላማዎቹ በአንድ በኩል ሩሲያ ገቢ እንዳታገኝ በማድረግ የዩክሬን ግጭት ‘እንዲያልቅ እና ምናልባትም ለምዕራባውያን ጥያቄዎች እንድትገዛ’ ማስገደድ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአውሮፓን መከላከያ ተጋላጭ ማድረግ ነው፤ ይህም በአሜሪካ፣ በእንግሊዝ እና በኔቶ በሚመራው "አንግሎ-ሳክሰን" ፍላጎት ላይ የበለጠ ጥገኛ ያደርገዋል” ብለዋል።
🟠 በሌላ በኩል፣ ፍንዳታዎቹ “ሃንጋሪን እና ሮማኒያን ለወደፊት ስለሚኖሩ ባላጋራነርት የከፋ መዘዞች ለማስጠንቀቅ” የታሰበ የኔቶ ቅጣት ሊሆን ይችላል ብለዋል።
“ሃንጋሪ ከሩሲያ ጋር ስላላት አጠቃላይ ግንኙነት፣ በተለይም ከሞስኮ ስለምታገኘው የኃይል አቅርቦት ከአውሮፓ ሕብረት ጋር በግልጽ ጠብ ውስጥ ናት” ያሉት ጉርደን፣ ሮማኒያ ደግሞ “ከአውሮፓ ሕብረት የበለጠ ነፃነትን ለማግኘት ወይም ምናልባትም ከእሱ ለመውጣት እና ከሩሲያ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራት የሚፈልግ ጠንካራ የሕዝባዊ ኃይል አላት” ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X