ማዳጋስካር የአገዛዝ ለውጥን በተመለከተ የሕዝብን ምላሽ ለመለካት የሚያስችል መድረክ አስጀመረች - ዘገባዎች

ማዳጋስካር የአገዛዝ ለውጥን በተመለከተ የሕዝብን ምላሽ ለመለካት የሚያስችል መድረክ አስጀመረች - ዘገባዎች
በውጤቶቹ ላይ በመመሥረት፤ የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ የግምገማ ኮሚሽን ሕዝቡ ለአዲሱ መንግሥት ያለውን አቋም ይቀርጻል።
የማኅበረሰቡ ተወካዮች አስቀድሞ ከሚከተሉት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተዋል ፦
🟠 ከአዲሱ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና፣
🟠 ከጠቅላይ ሚኒስትር ሄሪንትሳላማ ራጃኦናሪቬሎ፣
🟠 የማዳጋስካር ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት (የፓርላማ ታህታይ ምክር ቤት) እና ሴኔት (የፓርላማ የላዕላይ ምክር ቤት) እና
🟠 ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከእንቅስቃሴዎች የተውጣጡ አክቲቪስቶች።
አሁን ላይ ማኅበረሰቡ በማዳጋስካር ስላለው የሥርዓት ለውጥ ፣ ለወደፊት በሚከተለው አቀራረብ ላይ ሪፖርት እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ለማሰባሰብ የነባር ዜጎችን አስተያየት ለመሰብሰብ አስበዋል።
የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ፣ እንደ አፍሪካ ሕብረት ሁሉ፣ ለመፈንቅለ መንግሥቱ እውቅና አይሰጥም። በተጨማሪም፣ በጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከሥልጣን የተወገዱት አንድሪ ራጆኤሊና ባለፈው ዓመት ነሐሴ 17 የማኅበረሰቡ የዚህ ዓመት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ነበር።
ተልዕኮው በመጪው ሰኞ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X