ሩሲያ ለግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ቦታ የማብለያ አስረከበች - ሮሳቶም

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ ለግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ቦታ የማብለያ አስረከበች - ሮሳቶም
ሩሲያ ለግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ቦታ የማብለያ አስረከበች - ሮሳቶም - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.10.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ ለግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ቦታ የማብለያ አስረከበች - ሮሳቶም

“የኒውክሌር ማብለያ (ሬአክተር) ገጠማ በመጪው ሕዳር ወር መጀመሪያ ላይ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ ቡድኖቻችንም የፕሮጀክቱን ቁልፍ ምዕራፍ ለማሳካት ሳይሰለቹ እየሠሩ ነው” ሲሉ የግብፅ የኒውክሌር ኃይል ጣቢያዎች ባለሥልጣን ሊቀመንበር ሸሪፍ ሄልሚ ተናግረዋል።

የሩሲያ ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ እንዳመለከተው፤ የማብለያው ክብደት ከ330 ቶን በላይ ነው።

ፕሮጀክቱ በኩባንያው ንዑስ ድርጅት በሮሳቶም "አውቶሜትድ ኮንትሮል ሲስተምስ" እየተከናወነ ነው።

የኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አራት 1ሺህ 200 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ ቪቪኢአር-1200 ማብለያ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን፣ የሦስተኛ ትውልድ (ጄኔሬሽን III+) የደህንነት መስፈርቶችን ያሟላል። ሮሳቶም የኒውክሌር ነዳጅን ከማቅረብ በተጨማሪ፣ ለመጀመሪያዎቹ አስር ዓመታት ለሚሠሩ ሠራተኞች ሥልጠና በመስጠት እና ለተጠቀሙበት ነዳጅ የማጠራቀሚያ መፍትሄዎችን በማቅረብ ይረዳል ተብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0