ደቡብ አፍሪካ በሶቪዬት ድጋፍ በተቀጣጠለው ነፃነት የመጣውን የሰላምና የነጻነት ጉዞዋን ለማስቀጠል ትፈልጋለች - የኤኤንሲ ግምጃ ቤት ኃላፊ

ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ በሶቪዬት ድጋፍ በተቀጣጠለው ነፃነት የመጣውን የሰላምና የነጻነት ጉዞዋን ለማስቀጠል ትፈልጋለች - የኤኤንሲ ግምጃ ቤት ኃላፊ

የደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ግምጃ ቤት ኃላፊ ዶ/ር ግዌን ራሞክጎፓ፣ በደቡባዊ አፍሪካ ነጻነት ውስጥ የሶቪዬት እና የሩሲያ ሚናን በሚመለከት ከተዘጋጀ ዐውደ ርዕይ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገሩት፣ ለነፃነት የተደረገው ትግል በተናጠል  መንገድ አልተካሄደም። ዛሬ የሚደረገው የሰላምና ብልጽግና ፍለጋም እንዲሁ በተናጠል መልኩ መሆን የለበትም።

ዶ/ር ግዌን ራሞክጎፓ በኤኤንሲ እና አጋሮቹ በሆኑት በሶቭዬት ሕብረት፣ ቻይና፣ ኩባ እና ሌሎች መካከል በነበረው ታሪካዊ ትስስር ላይ አስተያየታቸውን አጋርተው የሚከተለውን አጽንዖት ሰጥተዋል፦

“ለሰላምና ለፍትሕ በሚደረገው ትግል ትብብራችንንና አጋርነታችንን የፈጠርን እኛ፤ ሰላምን መጠበቃችንን እና... ለዓለም ሕዝቦች የጋራ ብልጽግናን በጋራ ማስቀጠላችንን ለማረጋገጥ አሁንም ቢሆን እነዚያን ትብብሮች መፍጠር አለብን።”

አክለውም ወጣት ደቡብ አፍሪካውያን ከታሪክ ጥንካሬ እንዲያገኙ አሳስበዋል፦

“ታሪክ በጣም አስፈላጊ ነው... ስለዚህም ግጭቶችን ምን እንደፈጠራቸው፣ ግጭቶቹን ምን እንዳነሳሳቸው እና እነዚያን ፈተናዎች ተሻግረን ሰላምን እንዴት መፍጠር እንደቻልን ትምህርት እንድንወስድ ይረዳናል።”

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0