የዓለም ገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያን ጠንካራ የሪፎርም ፕሮግራም ትግበራ አደነቀ
21:23 23.10.2025  (የተሻሻለ: 22:34 23.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
የዓለም ገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያን ጠንካራ የሪፎርም ፕሮግራም ትግበራ አደነቀ
የኢትዮጵያ ልዑክ ከአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዋሽንግተን ውይይት አድርጓል።
በዚህ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት፣ የሥራ እድል ፈጠራ እና የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል ላይ ያተኮሩ ጠንካራ የሪፎርም ሥራዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የገንዘብ አስተዳደርን ለማጠናከር፣ የሀገር ውስጥ ሃብት ማሰባሰብን ለማጎልበት እና ቁልፍ መዋቅራዊ የሪፎርም ሥራዎች ለማፋጠን ቁርጠኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አይ ኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ ለሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ያመሠገኑም ሲሆን አበዳሪው ተቋም በበኩሉ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ለውጥ ለመርዳት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X