በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ የአሸባሪዎች ቡድን ጥቃት መክሸፉን የሀገሪቱ ጦር አስታወቀ
20:22 23.10.2025 (የተሻሻለ: 20:24 23.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ የአሸባሪዎች ቡድን ጥቃት መክሸፉን የሀገሪቱ ጦር አስታወቀ
ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ በአራት አካባቢዎች ጥቃቶችን ለመፈጸም ሞክረዋል ሲሉ የሰሜን ምስራቅ የጋራ ግብረ ኃይል የሚዲያ መረጃ መኮንን ሳኒ ኡባ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
“በሁሉም ቦታዎች ወታደሮቹ ጸንተው በመቆም በጀግንነት ተዋግተዋል፤ ጥቃቶቹንም በሙያዊ ብቃት በመመከት በአሸባሪዎቹ ላይ ከባድ፣ ወሳኝ እና ደቋሽ ጥቃት ፈጽመዋል” ሲሉ አስረግጠዋል።
ጥቃቱ የተጀመረው ሌሊቱን በቦርኖ እና ዮቤ ግዛቶች በሚገኙ በርካታ ወታደራዊ ቦታዎች ላይ መሆኑ ተጠቁሟል። የ "ሀዲን ካይ" ኦፕሬሽን ወታደሮች 50 ጥቃት አድራሾችን መግደልና መሳሪያዎቻቸውን መማረክ ችለዋል ሲሉ ኡባ አክለዋል።
ጥቃት አድራሾቹ የየትኛው አሸባሪ ቡድን አባላት እንደሆኑ ግን አልገለጹም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X