የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ 60 ዓመታት የማገልገል አቅም ባለው ዘመናዊው ቪ.ቪ.ኢ.አር 1200 ቴከኖሎጂ እንደሚገነባ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ 60 ዓመታት የማገልገል አቅም ባለው ዘመናዊው ቪ
የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ 60 ዓመታት የማገልገል አቅም ባለው ዘመናዊው ቪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.10.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ 60 ዓመታት የማገልገል አቅም ባለው ዘመናዊው ቪ.ቪ.ኢ.አር 1200 ቴከኖሎጂ እንደሚገነባ ተገለፀ

"በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈረመው የድርጊት መርሃ-ግብር ይህ ዘመናዊና ደህንነቱ የተጠበቀውን VVER-1200 ቴክኖሎጂ መሠረት ያደረገ የኃይል ማመንጫ ግንባታን ያመለክታል" ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭገኒ ተርኪን ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

በሰላማዊ የኒውክሌር ኃይል መስክ የሚደረገው ትብብር በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል "የኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ አጋርነት ዋና ምሰሶ" ሊሆን እንደሚችል አምባሳደሩ ገልፀዋል።

የVVER-1200 ቴከኖሎጂ ልዩ መለያዎች፦

በሮሳቶም የበለፀገ ሩሲያ ሠራሽ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

የቴክኖሎጂ ክፍሎቹ ለ60 ዓመታት ማገልገል ይቻላሉ፡፡

በግምት 1,200 ሜጋ ዋት አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።

ከቀደምት ቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋር ሲነጻጸር ወደ 36% የሚጠጋ የተሻሻለ ቅልጥፍና አለው።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0