የ2018 ብሔራዊ ምርጫ ግንቦት 24 እንዲካሄድ ምክረ ሃሳብ ቀረበ
17:30 23.10.2025 (የተሻሻለ: 17:34 23.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የ2018 ብሔራዊ ምርጫ ግንቦት 24 እንዲካሄድ ምክረ ሃሳብ ቀረበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚካሄድበትን ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር ለውይይት ማቅረቡ ተገልጿል፡፡
37 ተግባራት የሚከናወኑባቸውን ጊዜያት በቀን እና በወራት ከፋፍሎ ያስቀመጠው ቦርዱ ግንቦት 24 ድምፅ መስጫ፤ ሰኔ 3 ደግሞ ወጤት ይፋ ማድረጊያ ቀናት አድርጎ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ አስቀምጧል፡፡
በረቂቅ የግዜ ሰሌዳው የተካተቱ ሌሎች ተግባራት፦
በቴክኖሎጂ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ ከህዳር ወር አጋማሽ የካቲት መጨረሻ፣
መደበኛው የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት መጀመሪያ እስከ መጋቢት መጀመሪያ፣
በምርጫ የሚሳተፉ ዕጩዎች ምዝገባ ከታህሳስ መጀመሪያ እስከ ጥር መጀመሪያ፣
የምረጡኝ ቅስቀሳ ወይም የምርጫ ዘመቻ ከታህሳስ 10 እስከ ግንቦት 19፣
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ከሚያደርጋቸው ውይይቶች በኋላ ይፋዊ የምርጫ ቀኑን እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X