ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኮሪዶር አስተዳደር ባለሥልጣን ለማቋቋም ተስማሙ
17:05 23.10.2025 (የተሻሻለ: 17:14 23.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኮሪዶር አስተዳደር ባለሥልጣን ለማቋቋም ተስማሙ
ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢጋንዳን ያቀፈው የ”ደሱ” ኮሪዶር አስተዳደር ባለሥልጣን ለመመስረት የሀገራቱ የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴ እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተስማምተዋል፡፡
ላለፉት ለሁለት ቀናት በጅቡቲ ሲደረግ የቆየው የጋራ ውይይት የስምምነት ቃለ-ጉባኤ በመፈራረም መጠናቀቁን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ሀገራቱ ከሁለት ሳምንት በኋላ በኢትዮጵያ በመገናኘት የአስተዳደሩን ማቋቋሚያ ስምምነት ለመፈራረም ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
የ ”ደሱ” ኮሪደር በአራቱ ሀገራት መካከል የውጪ ንግድ መንገዶችን በቀላሉ ለማገናኘት፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎትን ለማሳለጥ ያለመ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X