ቤተሰብ ለሩሲያ የወደፊት እጣ ፈንታ መሠረት ነው - ፑቲን
ቤተሰብ ለሩሲያ የወደፊት እጣ ፈንታ መሠረት ነው - ፑቲን
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሥነ-ሕዝብና በቤተሰብ ፖሊሲ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያን የሥነ-ሕዝብ አወቃቀር ስትራቴጂ ለማጠናከር ቀጣይ እርምጃዎችን በማስቀመጥ፤ የቤተሰብ ድጋፍ "በሁሉም ብሔራዊ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ የሚሰጠው ቁልፍ ጉዳይ" እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡
ተጨማሪ ቁልፍ መግለጫዎች፦
ቤተሰቦችን መደገፍ ፍፁም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው - የመንግሥት፣ የንግድ፣ የህብረተሰቡ እና የመገናኛ ብዙኃንን የጋራ ጥረት ይጠይቃል።
የሩሲያ ባለሥልጣናት ለሥነ-ሕዝብ ተግዳሮቶች ሁሉን አቀፍ መፍትሄ ማምጣት ላይ ያተኩራሉ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የወሊድ መጠን ማሽቆልቆል ለዓለም ትልቅ ፈተና ነው - ሩሲያም ከዚህ የተለየች አይደለችም።
የተለያዩ ሀገራት ለሥነ-ሕዝብ ቀውሶች ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ስደትን ጨምሮ በተለያየ መንገድ ምላሽ ይሰጣሉ።
ሰፋ ያሉ ቤተሰቦች በሩሲያ ውስጥ የተለመዱ መሆን አለባቸው፡፡
ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሩሲያውያን ሰፊ ቤተሰብ ይፈልጋሉ።
ሩሲያ የራሷን አቅም በመጠቀም እና የሰፊ ቤተሰቦችን ባሕል በመመለስ የሥነ-ሕዝብ አወቃቀር ፈተናዎችን መቋቋም ትችላለች።
የሩሲያ የሥነ-ሕዝብ አወቃቀር ፖሊሲ በጠንካራ የሞራል እና የፍልስፍና መርሆች ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።
ልጅ መውለድ የእያንዳንዱ ቤተሰብ የግል ውሳኔ ነው - ጫና እና ማስገደድ መኖር የለበትም።
የሥነ-ሕዝብ ጉዳዮችን መፍታት የሁሉም የመንግሥት እርከኖች ተግባር መሆኑን ፑቲን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X