የማዳጋስካር መንግሥት ሙስናን እንደማይታገስ እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ
20:34 22.10.2025 (የተሻሻለ: 20:44 22.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማዳጋስካር መንግሥት ሙስናን እንደማይታገስ እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ
አዲሱ የማዳጋስካር መንግሥት የሕዝብን ሃብት ያለአግባብ ማዋልን በተመለከተ ከዚህ በፊት በተለየ ለሀገር ግንባታ የሚያደርገው ጥረት አካል አድርጎ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ በቅርቡ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ከሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያለ ማንኛውም ሰው ብሔራዊ ሀብት ወይም ገንዘብ ያለአግባብ በመጠቀም ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ፤ ደረጃው ወይም የቤተሰብ ግንኙነቱ ምንም ይሁን ምን የሰረቀውን ንብረት የሚመልስ እና ሕጋዊ እርምጃ የሚጠብቀው ይሆናል።
በሶስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ለሚጠበቅ የአስተዳደር ኦዲት፤ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ልዩ ፈቃድ ሳይኖራቸው ማዳጋስካርን ለቀው እንዳይወጡ ታግደዋል።
እነዚህ እርምጃዎች የሕዝብን ሀብት ሙሉ በሙሉ ለመከታተልና ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ለማረጋገጥ የተወሰዱ የሕዝብ አስተዳደር ቁጥጥር ማሻሻያ አካል ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አዲሱ የማዳጋስካር መንግሥት የዓለም አቀፍ ለጋሾችን እምነት ለመመለስ እየሠራ መሆኑን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X