ኢትዮ-ቴሌኮም ፓን-አፍሪካዊ የኤአይ ቋንቋ ስርዓት ለማልማት አህጉር አቀፍ ጥምረትን ተቀላቀለ
19:50 22.10.2025 (የተሻሻለ: 19:54 22.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮ-ቴሌኮም ፓን-አፍሪካዊ የኤአይ ቋንቋ ስርዓት ለማልማት አህጉር አቀፍ ጥምረትን ተቀላቀለ
ተቋሙ ከሞባይል ግንኙነቶች ዓለም አቀፍ ሲስተም (ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ) እና በርካታ የአፍሪካ ቴሌኮም ኦፕሬተሮች ጋር በመተባበር የአፍሪካን የቋንቋ እና የባሕል ብዝሃነት የሚያንጸባርቁ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ቋንቋ ሞዴሎችን ገቢር ያደርጋል።
“በአፍሪካ፣ ከአፍሪካ፣ ለአፍሪካ የኤ.አይ ቋንቋ ሞዴሎች” በሚል ራዕይ ጥምረት የፈጠሩት ተቋማት በአፍሪካ ቋንቋዎች እና በአህጉራዊ የመረጃ ስብስቦች የሠለጠኑ የኤ.አይ ስርዓቶችን ያለማሉ፡፡
ይህም መንግሥታት፣ የንግድ ድርጅቶች እና ማህበረሰቦች ከአፍሪካ እውነታዎች ጋር የተጣጣሙ መተግበሪያዎችን እንዲገነቡ ያስችላቸዋል ተብሏል።
የጥምረቱ ዓለማ በአፍሪካ የኤ.አይ አጠቃቀም፦
የመረጃ፣
የኮምፒውተር አቅም፣
የሰው ኃይል እና
የፖሊሲ ክፍተቶችን መሙላት ነው።
አሁን ያሉት ዓለም አቀፍ የኤ.አይ ሞዴሎች በአብዛኛው ጥቂት ዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን የሚደግፉ በመሆናቸው የአፍሪካ ከ2 ሺህ በላይ ቋንቋዎች ተገቢውን ውክልና እንዳላገኙ ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ በጥናቱ አረጋግጧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X