“የድህረ ቅኝ ግዛት ተጽዕኖን መዋጋት የሚቻለው በሃሳብ ስለሆነ የስፑትኒክ ሚና ምትክ የለውም” - የፖለቲካ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“የድህረ ቅኝ ግዛት ተጽዕኖን መዋጋት የሚቻለው በሃሳብ ስለሆነ የስፑትኒክ ሚና ምትክ የለውም” - የፖለቲካ ባለሙያ
“የድህረ ቅኝ ግዛት ተጽዕኖን መዋጋት የሚቻለው በሃሳብ ስለሆነ የስፑትኒክ ሚና ምትክ የለውም” - የፖለቲካ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.10.2025
ሰብስክራይብ

“የድህረ ቅኝ ግዛት ተጽዕኖን መዋጋት የሚቻለው በሃሳብ ስለሆነ የስፑትኒክ ሚና ምትክ የለውም” - የፖለቲካ ባለሙያ

ስፑትኒክ በአፍሪካ መዲና አገልግሎት መስጠት መቻሉ ዲሞክራሲን፣ መልካም አስተዳደርን እና በምዕራቡ ዓለም የተቃኘውን ሂደት ሚዛናዊ ለማድረግ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የፓለቲካ ሳይንስ ምህሩ እንዳለ ንጉሴስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

አህጉሪቱ ችግሮቿን በራሷ ለመፍታት እና ልማቷን ለማጎልበት በምታደርገው ሂደት የሚዲያው ሚና የጎላ ይሆናልም ብለዋል፡፡

“በሩዋንዳም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ግጭት ጠንሳሾቹ ብዙዎቹ በምዕራቡ ዓለም የሚዘወሩ ሚዲያዎች ናቸው፡፡ ይሄ ምንም የሚካድ ነገር አይደለም፤ ስለዚሀ አደገኛ ግጭቶች እንዲከሽፉ በማድረግ ረገድ ሀሳብ በሚዲያ በኩል ተደራሽ ስለሚሆን ስፑትኒክ ወደ ኋላ ማለት የለበትም፤ አሁን ያለው ሚና የላቀ ነው” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ስፑትኒክ አፍሪካ ባለፈው ዓመት የካቲት ወር በአዲስ አበባ ሁለገብ ኤዲቶሪያል ማዕከሉን ከከፈተ ወዲህ ተደራሽነቱ እየጨመረ መምጣቱን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ጋር በሞስኮ በነበራቸው ውይይት መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0