ሁለት የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ንግግር ላይ ናቸው - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር
17:47 22.10.2025 (የተሻሻለ: 17:54 22.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሁለት የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ንግግር ላይ ናቸው - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር
ኡልያኖቭስክ እና አውቶቫዝ የአውቶሞቢል ፋብሪካዎች የሀገሪቱን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምህዳር እያጠኑ እንደሚገኙ አምባሳደሩ ኢቭጌኒ ተርኪን ለሩሲያ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡
“ይህ ሂደት የፕሮጀክቶቹን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ለማረጋገጥ ጥልቅ የገበያ እና የቴክኒክ ምርምር ማድረግን ያካትታል። ድርድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ ውጤቱ የሩሲያ መኪኖች በኢትዮጵያ መንገዶች የሚገባቸውን ቦታ እንዲያገኙ ወደሚያስችሉ ውሳኔዎች እንደሚመራ እንጠብቃለን" ብለዋል፡፡
በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ካሉት እጅግ ተስፋ ሰጪ የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፎች ውስጥ አንዱ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ እንደሆነ አምባሳደሩ አክለዋል።
"ወደ 130 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ የሚይዘው ሰፊው የኢትዮጵያ ገበያ የሩሲያ አምራቾች ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ነው።”
ከሴንት ፒተርስበርግ ትራክተር ፋብሪካ የሙከራ ትራክተሮች እንደተላኩ እና "ላዳ ኤክስፖርት" የተባለው ኩባንያ ከ "ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ" ጋር የአጋርነት ግንኙነት መመስረቱም ነው የተመላከተው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X