በካሜሩን ብሔራዊ ምርጫ ውጤት ዙሪያ በተነሳ ተቃውሞ ውጥረት ነግሷል
በካሜሩን ብሔራዊ ምርጫ ውጤት ዙሪያ በተነሳ ተቃውሞ ውጥረት ነግሷል
የሕገ-መንግሥት ምክር ቤቱ የጥቅምት 2 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ይፋ እስከሚያደርግ እየተጠባበቀች ያለችው ካሜሩን፤ ብጥብጥ ውስጥ ትገኛለች። ከብሔራዊ ቆጠራ ኮሚሽን በወጡ ጊዜያዊ ውጤቶች መሠረት፤ የ92 ዓመቱ እና ለ43 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት ፖል ቢያ 53.66 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል።
ሆኖም፤ የቀድሞ ሚኒስትር እና ተቃዋሚ ፓርቲ የተቀላቀሉት ዋና ተፎካካሪያቸው ኢሳ ቺሮማ ባካሪ እራሳቸውን አሸናፊ ብለው ያወጁ ሲሆን የተሰጣቸውን የ35.19 በመቶ ውጤት በመቃወም በግምት 55 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ እንዳገኙ ተናግረዋል።
በአፍሪካ ሚዲያዎች ዘገባ መሠረት ፕሬዝዳንት ቢያ ተቃዋሚ ፓርቲው ድላቸውን እንዲቀበል፤ በምላሹ ለቺሮማ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ በማቅረብ ቀውሱን ለማርገብ ጥረት ቢያደርጉም ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የቺሮማ ደጋፊዎች "የ2025 ዩኒየን ፎር ቼንጅ" ጥምረት አባላት፤ የምርጫ ውጤቱን የማጭበርበር ሙከራዎችን አውግዘው የሕገ-መንግሥት ምክር ቤቱ "የድምፅ መስጫ ሳጥኑን ትክክለኛ እውነት እንዲያስመልስ" ጥሪ አቅርበዋል።
በተለያዩ ከተሞች የተደረጉት የተበታተኑ ሰልፎች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ የአለመተማመን ስሜት ታጅበው የምርጫ ማጭበርበር ክሶች የተንፀባረቁበት እንደነበር ተገልጿል።
የተቃውሞ ሰልፎቹ ማዕከላት፦
ጋሩዋ (ሰሜን፣ የቺሮማ ይዞታ)፦
🟠 ማክሰኞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣት ደጋፊዎች እጯቸውን ለመደገፍ አደባባይ ወጥተዋል።
🟠 ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር ከባድ ግጭቶች የተፈጠሩ ሲሆን የድንጋይ ውርወራ፣ የማስጠንቀቂያ ጥይቶች እና አንድ የተረጋገጠ ሞት እንደነበር ተዘግቧል።
🟠 ከ2 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ያሏት ከተማዋ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች።
🟠 ቺሮማ ለሁለት ሳምንታት በቤታቸው ተወስነው የቆዩ ሲሆን የጸጥታ ኃይሎችም በእጩው ቤት ዙሪያ ተሰማርተዋል።
🟠 በኢሳ በቺሮማ ደጋፊዎች እና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ አንድ የፖሊስ ተሽከርካሪ በእሳት ተቃጥሏል።
ያውንዴ (ዋና ከተማ)፦
🟠 በጺንጋ ሰፈር ፖል ቢያ ሥልጣን እንዲለቁ ለመጠየቅ የቺሮማ ደጋፊዎች ያካሄዱት ሰልፍ በአንድ ሰዓት ውስጥ በአስለቃስሽ ጭስ ተበትኗል።
ዱዋላ (የኢኮኖሚ ዋና ከተማ)፦
🟠 በኒው ቤል ሠፈር ተመሳሳይ የግርግር ክስተቶች ተስተውለዋል።
🟠 የግዛት አስተዳደር ሚኒስትር ፖል አታንጋ ንጂ በርካታ እስሮች መፈፀማቸውን አስታውቀዋል።
በእነዚህ ሶስት ከተሞች የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ላይ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል።
የ2025 ዩኒየን ፎር ቼንጅ ጥምረት፤ ሐሙስ ዕለት ከጠዋቱ 6 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ድረስ ድላቸውን "በሰላም ለማክበር" የሥራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ ለአክቲቪስቶች እና ደጋፊዎች ጥሪ አቅርቧል።
የካሜሩን ሕገ-መንግሥት ምክር ቤት የመጨረሻውን ውጤት ሐሙስ ዕለት ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X