በኢትዮጵያ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች ለገበያ ቀረቡ
16:27 22.10.2025 (የተሻሻለ: 16:34 22.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች ለገበያ ቀረቡ
ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር ከቻይናው የከባድ መኪና አምራች ሻክማን ኩባንያ ጋር በጋራ በመሆን ተሽከርካሪዎቹን ለመጀመሪያ ግዜ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋውቀዋል፡፡
ድርጅቱ ከሻክማን ኩባንያ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ መኪኖችን በመረከብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማቅረብ በትናንትናው ዕለት ስምምነት የፈፀመ ሲሆን በቅርቡም 150 ተሽከርካሪዎች እንደሚገቡ ተገልጿል።
ቤአኤካ በመጀመሪያ ዙር የምርት ምዕራፍ በሀገር ውስጥ 1 ሺህ 500 በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠምም አቅዷል፡፡
በቅርቡ በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል የካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ የመጀመሪያ ዙር ምረት መጀመሩን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነዳጅ የሚጠቀሙ ከባድ መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደተከለከለ መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X