የትግራይ ኃይሎች በክልሉ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ወቅት በፈጠሩት የመንገድ መዘጋጋት ይቅርታ ጠየቁ
15:32 22.10.2025 (የተሻሻለ: 15:34 22.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የትግራይ ኃይሎች በክልሉ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ወቅት በፈጠሩት የመንገድ መዘጋጋት ይቅርታ ጠየቁ
ወታደሮቹ ባሳለፍነው ሳምንት ትክክለኛ ነው ያሉትን ቅሬታ ለማቅረብ ለአምስት ቀናት ያካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ በተገቢው መንገድ እንዳልተከናወነ አምነዋል፡፡
"ሠራዊት 22" በመባል የሚታወቀው ቡድን አባላት የወሰዱት እርምጃ ለሠራዊቱም ሆነ ለሲቪሉ ሕዝብ አደጋ የፈጠረ እንደነበር በመቀበል፣ በሰልፉ ወቅት ለተፈጠረው መስተጓጎል እና እንግልት መጸጸታቸውን በመግለፅ ተመሳሳይ ድርጊቶችን ላለመድገም ቃል ገብተዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
የትግራይ ኃይሎች የተሻለ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ለመጠየቅ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የክልሉን ዋና ዋና መንገዶች መዝጋታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X