አፍሪካ የሚፈልሱ ዜጎቿን ለማቆየት መዳሰስ፣ መጨበጥ የሚችል የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሽግግር ስርዓት ልትዘረጋ ይገባል - ባለሙያ
15:08 22.10.2025 (የተሻሻለ: 15:14 22.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካ የሚፈልሱ ዜጎቿን ለማቆየት መዳሰስ፣ መጨበጥ የሚችል የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሽግግር ስርዓት ልትዘረጋ ይገባል - ባለሙያ
አፍሪካ በእቅፏ ያሉ ዜጎቿ እንዳይሄዱ፤ የሠለጠኑትንም ለማምጣት የሚያስችል ልዩ እቅድ እና የማትጊያ ማዕቀፍ ያለው ስትራቴጂ መተግበር እንደሚኖርባት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያው ዶ/ር ታምራት ዘላለም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
“የደህንነት ዋስትና አናሳ ስለሆነ መሰደድ አሁንም ቢሆን ለተወሰኑ ዓመታት ብቸኛ አማራጭ ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር ነው። ይበረታታል ወይ? አይበረታታም። ሊቀር ይገባል። ያን ለማስቀረት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ባለድርሻዎች፤ በጋራ ሆነው አንድ ጊዜ ብቻ ወይም በዘመቻ ሳይገደቡ በጊዜ የለንም መንፈስ ተከታታይነት ያለው ሥራ ሊከውኑ ይገባል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ቀጣዩ ትውልድ መሰደድን አማራጭ ሳያደርግ በሀገሩ ሰርቶ መለወጥን፣ ለማህበረሰቡ ሠርቶ ማለፍን እንደ አንድ የጀግንነት ማሳያ እየቆጠረ ማደግ ሲጀምር ይህ እውን ሊሆን እንደሚችል አፅንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም ባለሙያው ሂደቱን ለማፍጠን፦
በትምህርት ስርዓቱና
በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት የተቀናጀ ሥራ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
አፍሪካ በዓመት 70ሺ ገደማ አምራች የሰው ኃይል እንደምታጣ የአፍሪክ ኅብረት መረጃን አጣቅሰው ባለሙያው አመላክተዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X