ኢትዮጵያ በብሪክስ የቴክኖሎጂ ውድድር በሰባት ዘርፎች ተሸላሚ ሆነች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በብሪክስ የቴክኖሎጂ ውድድር በሰባት ዘርፎች ተሸላሚ ሆነች
ኢትዮጵያ በብሪክስ የቴክኖሎጂ ውድድር በሰባት ዘርፎች ተሸላሚ ሆነች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በብሪክስ የቴክኖሎጂ ውድድር በሰባት ዘርፎች ተሸላሚ ሆነች

በ15 ዘርፎች በተካሄደው የብሪክስ ቤልት ኤንድ ሮድ የቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፎ ያደረገው የኢትዮጵያ ልዑክ አራት የብር እና ሶስት የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘት ችሏል፡፡

የብር ሜዳሊያ ያገኙት የፈጠራ ሥራዎች፦

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሉሲ፦ በሮቦቲክስ እና በኢንተርኔት መር ቴክኖሎጂዎች (አይኦቲ) ውህደት የላቀ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት፣

ዲጂታል ግብርና፦ የዘመነ የግብርና ሮቦት ሲስተም በሳቪ አጠቃላይ ንግድ ኃ.የተ.የግ.ማ.፣

የላቀ ማምረቻ፦ በራሱ ምርት መደርደር የሚችል የሮቦት ክንድ፣

ዘመናዊ የውሃ አስተዳደር፦ የውሃ መፍሰስን የሚያስቀር ተንቀሳቃሽ የውሃ ቫልቭ፡፡

የነሐስ ሜዳሊያ ያሸነፉ የፈጠራ ሥራዎች፦

አረንጓዴ ኃይል፦ ኢትዮ ታዳሽ የነዳጅ አማራጭ፣

ዲጂታል ግብርና፦ ኢንተርኔት መር ቴክኖሎጂዎችን (አይኦቲን) መሠረት ያደረገ የዘመነ የመስኖ ክትትልና መቆጣጠሪያ ስርዓት፣

የላቀ የማምረት ሥራ፦ ከፊል አውቶማቲክ በሹራብ ጨርቅ ጭረት መዘርጊያ ማሽን፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል “አሸናፊዎች የድካማቹን ፍሬ መቅመስ ስለጀመራቹ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!” ሲሉ መልዕክታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አጋርተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በብሪክስ የቴክኖሎጂ ውድድር በሰባት ዘርፎች ተሸላሚ ሆነች
ኢትዮጵያ በብሪክስ የቴክኖሎጂ ውድድር በሰባት ዘርፎች ተሸላሚ ሆነች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.10.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0