አፍሪካ ዘላቂ ልማት እንድታሳካ ፖለቲካዊ ሉዓላዊነቷን ልታረጋግጥ ይገባል - ምሁር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ ዘላቂ ልማት እንድታሳካ ፖለቲካዊ ሉዓላዊነቷን ልታረጋግጥ ይገባል - ምሁር
አፍሪካ ዘላቂ ልማት እንድታሳካ ፖለቲካዊ ሉዓላዊነቷን ልታረጋግጥ ይገባል - ምሁር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.10.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካ ዘላቂ ልማት እንድታሳካ ፖለቲካዊ ሉዓላዊነቷን ልታረጋግጥ ይገባል - ምሁር

አህጉሪቱ ወጥ የሆነ የእድገት አቅጣጫ ሊኖራት እንደሚገባም በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ፍራፊስ ሃይሌ (ዶ/ር) ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡

“ፖለቲካዊ ሉዓላዊንት ካለን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ እንችላለን። የሚጠበቅብን ያልተቆራረጠ፣ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማይቆም ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪያዊ እድገት እንዲኖረን ማድረግ ነው። አረንጓዴ ቴክኖሎጂ፣ ሰርኩላር ኢኮኖሚ ላይ መሥራት ከቻልን ኢንዱስትሪና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነታችንን ማስጠበቅ የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም። ይሄን እንደ ራዕይ መያዝ አለብን።”

ሲያክሉም ኢኮኖሚን ዘርፈ ብዙ ማድረግ ከጥገኝነት የተላቀቀ ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደሚያስችል አንስተዋል፡፡

“ሌላኛው በተለይ ግብርና ላይ ጥገኛ ከመሆን ኢኮኖሚውን ወደ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቴክኖሎጂ ሰፋ ማድረግ፤ ይሄ ሁሉ ደግሞ አንድ ላይ ሲደመር ከዓለም ገበያ መዋዠቅ ይጠብቀናል፤ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት ያስችለናል” ብለዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0