ሩሲያ ዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን ከኪዬቭ ጥቃት ለመጠበቅ የዓለም አቀፉን የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እርዳታ ጠየቀች
11:11 22.10.2025 (የተሻሻለ: 11:14 22.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን ከኪዬቭ ጥቃት ለመጠበቅ የዓለም አቀፉን የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እርዳታ ጠየቀች
ሞስኮ የኒውክሌር ማመንጫውን የውጭ ኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ለመመለስ የተኩስ አቁም እንዲመቻች ድርጅቱን መጠየቋን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለስፑትኒክ አስታውቋል።
አስቸጋሪ እና ፈታኛ ምክክር ከተደረገ በኋላ ይህን ለማድረግ ከዩክሬን የጸጥታ ዋስትና መገኘቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው በዩኒቶች ብዛትና በተገጠመለት አቅም በአውሮፓ ትልቁ ሲሆን እያንዳንዳቸው አንድ ጊጋዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው ስድስት ዩኒቶች አሉት።
በጥቅምት 2014 የዛፖሮዥዬ ክልል እና የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው የሩሲያ አካል መሆን ችለዋል። በዩክሬን ጥቃት በተደጋጋሚ ኢላማ የሚደረገው የኃይል ማመንጫው፤ በቅርቡም ጉዳት ደርሶበት በአቅራቢያው ወደምትገኘው ከተማ የሚተላለፈው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጧል ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X