ኬንያ እና ሴኔጋል ታሪካዊ ከቪዛ-ነጻ የጉዞ ስምምነት ተፈራረሙ
10:30 22.10.2025 (የተሻሻለ: 10:34 22.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኬንያ እና ሴኔጋል ታሪካዊ ከቪዛ-ነጻ የጉዞ ስምምነት ተፈራረሙ
ስምምነቱን ተከትሎ የሁለቱም ሀገራት ዜጎች እስከ 90 ቀናት ድረስ ያለቪዛ መጓዝ ይችላሉ። የዲፕሎማቲክ እና መደበኛ ፓስፖርት ያላቸው ሰዎች ያለቪዛ ወደ የትኛውም ሀገር መግባት፣ መቆየት እና መሸጋገር ይችላሉ።
ፕሬዝዳንት ሩቶ የትብብሩን ሰፋ ያለ ራዕይ በንግግራቸው አጽንኦት ሰጥተውታል፦
“በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት በሰላም፣ በፀጥታ፣ በኃይል፣ በንግድ እና በውጭ ጉዳይ ያለንን የጋራ ትብብር አረጋግጠናል። ይህ ስምምነት በሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር ያጠናክራል እንዲሁም ቱሪዝምንና ንግድን ያሳድጋል” ብለዋል።
ከቪዛ ስምምነቱ ባሻገር መሪዎቹ የንግድ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ፣ የትራንስፖርት እና ዲጂታል መሠረተ ልማቶችን ለማሳደግ እንዲሁም ኬንያ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጀት በተሰናዳችበት ወቅት በስፖርት ልማት ለመተባበር ቃል ገብተዋል።
በተጨማሪም ፍትሐዊ ውክልና ለማረጋገጥ እና በዓለም አቀፍ አስተዳደር ውስጥ የአፍሪካ ድምጾች እንዲሰሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማትን ስለማሻሻል ተወያይተዋል።
ፕሬዝዳንት ባሲሩ ፋዬ ጉብኝታቸውን አስመልክቶ በኤክስ ገፃቸው ላይ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦
“ወደ ኬንያ ያደረግኩት ይፋዊ ጉብኝት በእርካታ ተጠናቋል...ይህ ጉብኝት በሴኔጋል እና በኬንያ መካከል ያለውን ወንድማዊ የወዳጅነት ግንኙነት ለማጠናከር እና ለአዲስ የትብብር አድማስ መንገድ ለመክፈት አስተዋፅዖ አድርጓል።”
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

