የጋዛ ስምምነት ሂደት ከተጠበቀው በላይ እየሄደ ነው - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት

ሰብስክራይብ

የጋዛ ስምምነት ሂደት ከተጠበቀው በላይ  እየሄደ ነው - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት

ሁሉም ሀገራት ከድህረ ጦርነቱ በኋላ ጋዛን መልሶ ለመገንባት እገዛ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ጄ.ዲ. ቫንስ የእስራኤል-ሀማስ ስምምነት ሁለተኛ ምዕራፍ ውይይትን ለመጀመር እስራኤል ሲደርሱ

በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

"ይህ የገንዘብ ድጋፍ፣ የመልሶ ግንባታ እርዳታ ወይም የዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ሊሆን ይችላል፤ የሰላም ሂደቱን አፈጻጸም እና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ከተለያዩ አካላት ጋር መነጋገር" ሲሉም አክለዋል።

የትራምፕ ልጅ ባለቤት ጃሬድ ኩሽነር እና የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ሰኞ ዕለት እስራኤል ደርሰዋል። ጉብኝታቸው መስከረም 30 ተግባራዊ የሆነው የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሷል አየተባለ ባለበት ወቅት የመጣ ነው።

እሁድ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ሀማስ በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ተኩስ በመክፈት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል ሲል ከሷል። የእስራኤል ጦር በአጸፋው በጋዛ የሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ የሀማስ ኢላማዎችን አጥቅቷል።

ℹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የግብፅ ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ፣ የኳታር አሚር አል ታኒ እና የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን ጥቅምት 3 ቀን ተፈራርመዋል። በዚህም ሀማስ 20 ታጋቾችን እንዲለቅ እና እስራኤልም ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንድትፈታ ሆኗል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0