ኡጋንዳ ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ቀን ጥር 7 እንዲሆን ወሰነች

ሰብስክራይብ

 ኡጋንዳ ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ቀን ጥር 7 እንዲሆን ወሰነች

በቀጣዩ ምርጫ ለተጨማሪ የሥልጣን ዘመን የሚወዳደሩትና ከ1978 ጀምሮ ሥልጣን ላይ የሚገኙት የ80 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዩሪ ሙሴቬኒ ያለፉትን ምርጫዎች አጭበርብረዋል በሚል ክስ ካቀረቡባቸው የ43 ዓመቱ ሙዚቀኛ እና ፖለቲከኛ ቦቢ ዋይን ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ በተቃዋሚው የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጎታል፡፡

 ስድስት ሌሎች እጩዎችም በውድድሩ ውስጥ የሚሳተፉበት ሲሆን ኡጋንዳውያን ፕሬዝዳንቱን እና የፓርላማ አባላትን ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ናቸው።

የሙሴቬኒ ደጋፊዎች ለሀገሪቱ መረጋጋትና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ሲገልጹ፤ ተቃዋሚዎች ግን ጭቆናን፣ ሙስናን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይጠቅሳሉ።

 መንግሥት በሚቀጥለው ዓመት የሚጀመረው የድፍድፍ ነዳጅ ምርት ወደ ውጭ በመላክ የሀገሪቱን የዕድገት ምጣኔ እንደሚያሳድግ ይጠብቃል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0