የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት በደቡብ ምስራቅ እስያ ለሚያደርጉት የሶስት ሀገራት ጉብኝት ጉዞ ጀመሩ
19:19 21.10.2025 (የተሻሻለ: 19:24 21.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት በደቡብ ምስራቅ እስያ ለሚያደርጉት የሶስት ሀገራት ጉብኝት ጉዞ ጀመሩ
ሲሪል ራማፎሳ ከጥቅምት 12 እስከ 18 በሚቆየው የውጭ ጉዟቸው በኢንዶኔዢያ እና ቬትናም የሀገራት ጉብኝት፥ አስከትሎም በማሌዢያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በኢንዶኔዢያ እና ቬትናም፦ ፕሬዝዳንቱ ግብርና፣ ቱሪዝም እና መከላከያ ባሉ ዘርፎች ትብብር፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስፋት ላይ የሚያተኩሩ የሁለትዮሽ ውይይቶች ያደርጋሉ።
በማሌዢያ፦ ራማፎሳ በ47ኛው የደቡብ ምስራቅ እስያ መንግሥታት ጉባኤ ላይ የሊቀመንበሩ ተጋባዥ እንግዳ በመሆን የሚሳተፉ ሲሆን ይህም ደቡብ አፍሪካ የደቡብ ምስራቅ እስያ መንግሥታት የዘርፍ ውይይት የአጋርነት ሚናዋን ያጎላል።
እንደ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤቱ ገለጻ ጉብኝቱ የሚከተሉትን ለማድረግ ያለመ ነው፦
▫የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ማጠናከር፣
▫የንግድ አጋርነቶችን ማብዛት፣
▫ደቡብ አፍሪካ ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበ ካለው የደቡብ ምስራቅ እስያ ክልል ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ተሳትፎ ማጠናከር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X