ፈረንሳይ እና ጀርመን አፍሪካን ለማተራመስ፤ ጥላቻ ቀስቃሾችን እያበረታቱ ነው - የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት
18:10 21.10.2025 (የተሻሻለ: 18:14 21.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፈረንሳይ እና ጀርመን አፍሪካን ለማተራመስ፤ ጥላቻ ቀስቃሾችን እያበረታቱ ነው - የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፈረንሳይ እና ጀርመን አፍሪካን ለማተራመስ፤ ጥላቻ ቀስቃሾችን እያበረታቱ ነው - የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት
ፓሪስ "ከሃዲ" አፍሪካውያንን እየደገፈች ነው በማለት በይፋ የከሰሱት ቴዎዶሮ ንጉዌማ ኦቢያንግ ማንጌ፤ በርሊን እንዲህ አይነቱን ዘመቻ በመቀላቀሏ ውግዘት ሰንዝረዋል።
"ሰላምን እንዲያደፈርሱ እና የራሳቸውን ባሕልና ወንድም እንዲቃወሙ" ለጥቅም የተገዙ ግለሰቦችን በማነሳሳቷ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ፈረንሳይ ላይ "ቁጣቸውን" ገልጸዋል።
ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ የሚኖር "ሀገሩን የካደ የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜጋ"፤ ከማድሪድ የጀርመን አምባሳደር እና ከከፍተኛ የፈረንሳይ ዲፕሎማት ጋር በመሆን የፈጠረውን ክስተት ጠቅሰዋል።
ባለሥልጣኑ የትኛውን ክስተት ማለት እንደፈለጉ ባይገልጹም፤ ይፋዊ መግለጫቸው የተሰጠው የኢኳቶሪያል ጊኒ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አልፍሬዶ ኦኬንቬ ለፍራንኮ-ጀርመን የሰብዓዊ መብት ሽልማት ከታጨ በኋላ ነው።
ፈረንሳይ ሀገራቸውን ለማተራመስ "ስልታዊ የትንኮሳ ፖሊሲ" እየተከተለች ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ፓሪስ በማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ ባሉ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ላይ ይህንን ዘዴ ተጠቅማበታለች ብለዋል።
"አፍሪካ እንደዚህ አይነት ሴራዎች መረዋታል!" ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X