ወደሀገር ውስጥ ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች 99 በመቶዎቹን የኤሌክትሪክ ለማድረግ ታቅዷል - የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር
17:03 21.10.2025 (የተሻሻለ: 17:04 21.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱወደሀገር ውስጥ ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች 99 በመቶዎቹን የኤሌክትሪክ ለማድረግ ታቅዷል - የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ወደሀገር ውስጥ ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች 99 በመቶዎቹን የኤሌክትሪክ ለማድረግ ታቅዷል - የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር
አሁን ላይ በሀገሪቱ ከሚገኙ አጠቃላይ ተሽከርካሪዎች ሰባት በመቶ ያህሉን የሚሸፍኑ 115 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ከ10 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን በላይ ለማድረስ መታቀዱን ጠቁመው፤ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉንም አንስተዋል።
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በቀላሉ እንዲገቡ ሂደቱን የማቅለልና ተደራሽነታቸውን ለማስፋት እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አሰተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X