ኢትዮጵያ ለቻይና መንግሥት የምትከፍለውን የ5.38 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በከፊል ወደ ቻይና ገንዘብ (ዩዋን) ለመቀየር ንግግር ጀመረች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ለቻይና መንግሥት የምትከፍለውን የ5
ኢትዮጵያ ለቻይና መንግሥት የምትከፍለውን የ5 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ለቻይና መንግሥት የምትከፍለውን የ5.38 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በከፊል ወደ ቻይና ገንዘብ (ዩዋን) ለመቀየር ንግግር ጀመረች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካለኝ በቅርቡ በቤጂንግ ባደረጉት ጉብኝት ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ እና ከቻይና ሕዝብ ባንክ ጋር በዚሀ ረገድ ውይይት መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ጥያቄዋ ቀደም ሲል ለተመጣጣኝ ክፍያ ወደ ዩዋን ፊታቸውን እያዞሩ ያሉትን እንደ ስሪላንካ፣ ሃንጋሪ እና ኬንያ ያሉ ሀገራትን ተቀላቅላለች፡፡

“ቻይና አሁን ለኛ በጣም አስፈላጊ አጋር ናት፤ የንግድና ኢንቨስትመንት መጠኑ እያደገ ነው፡፡ ስለዚህ የተወሰነ የመገበያያ ልውውጥ መኖሩ ምክንያታዊ ነው፡፡ በትክክልም ይህ በሂደት ያለ ነገር ነው፤ በይፋ ጠይቀናል እናም እየሠራንበት ነው” ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ከዓለም አቀፋ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ትይዩ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0