ማላዊ ነፃ ትምህርት እና ርሃብን ለመዋጋት የአደጋ ግዜ የምግብ አቅርቦት ይፋ አደርገች
15:17 21.10.2025 (የተሻሻለ: 15:24 21.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ማላዊ ነፃ ትምህርት እና ርሃብን ለመዋጋት የአደጋ ግዜ የምግብ አቅርቦት ይፋ አደርገች
ከመጪው ጥር 2026 ጀምሮ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለሁሉም የማላዊ ዜጎች ነፃ እንደሚሆን አዲስ ተሿሚው ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሪካ አስታውቀዋል።
"ወላጆች አሁን ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ላለመላክ ምንም ምክንያት አይኖራቸውም" ሲሉ የተናገሩት ሙታሪካ፤ ትምህርት ለብሔራዊ ልማት መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ስለ ሀገሪቱ የምግብ ቀውስ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ የምግብ እጥረት ላለባቸው ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ አቅርቦት ከውጭ እንደሚገባ ይፋ አድርገዋል፡፡ መንግሥት ከአራት ሚሊዮን በላይ የምግብ እጥረት ያለባቸውን ሰዎች ለመመገብ 200ሺህ ቶን በቆሎ ከዛምቢያ እየገዛ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንቱ ስምምነቱን ለመፈፀም "ሁሉም ነገር ዝግጁ" እንደሆነና የግብርና ሚኒስትሩም በዛምቢያ ቅድመ ዝግጅቶች እያጠናቀቁ እንደሚገኙ ለዜጎቻቸው አረጋግጠዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X