ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈረመው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ስምምነት በቀጣናው ቀዳሚ የኃይል አቅራቢነቷን እንደሚያጠናክር ተስፋ ታደርጋለች - ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለስፑትኒክ አፍሪካ
ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈረመው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ስምምነት በቀጣናው ቀዳሚ የኃይል አቅራቢነቷን እንደሚያጠናክር ተስፋ ታደርጋለች - ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለስፑትኒክ አፍሪካ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከላቭሮቭ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታን ለማካሄድ ከሩሲያ ጋር የተደረሰው የቅርብ ጊዜ ስምምነትን የተመለከቱ በርካታ ቁልፍ ነጥቦችን አብራርተዋል።
🟠 የቀጣናዊ ሚናን ማሳደግ፦ ፕሮጀክቱ በሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ከመሆኑም በላይ የላቀ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ያስተዋውቃል። ይህ ኢትዮጵያን በክልሉ የኃይል ፈጠራ ዘርፍ ግንባር ቀደምት እንድትሆን ያደርጋታል።
🟠 የኤልክትሪክ ኃይል ወደ ውጭ ስለመላክ፦ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ እንደ ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ላሉ ጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል መላክ ጀምራለች። የኒውክሌር ኃይል መጨመር፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ውጭ መላክን የበለጠ ለማጠናከር እና የቀጣናዊ ውህደትን ለማሳደግ ያለመ ነው።
🟠 የኢንዱስትሪ ልማት መነሳሳት፦ ንጹህ ኃይል ከማቅረብ ባለፈ አዲሱ የኒውክሌር ተቋም የኢትዮጵያን ሰፋፊ የኢንዱስትሪ ልማት እና በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ቴከኖሎጂዎችን የማዘመን ጥረቶችን ከማፋጠን ጋር የተጣጣመ ነው።
🟠 የቴክኖሎጂ እድገት፦ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃብቶችን እና አዳዲስ የኒውክሌር መፍትሄዎችን አጣምሮ በመጠቀም፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የወደፊት እድገት ውስጥ ወሳኝ በሆኑት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ግንባር ቀደም መሆን ትፈልጋለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X