ጋና በሕገ-ወጥ የደን ሥራዎች ላይ በተደረገ ዘመቻ የማዕድን ቁፋሮ መሳሪያዎችን መያዟ ተዘገበ
20:07 20.10.2025 (የተሻሻለ: 20:14 20.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጋና በሕገ-ወጥ የደን ሥራዎች ላይ በተደረገ ዘመቻ የማዕድን ቁፋሮ መሳሪያዎችን መያዟ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጋና በሕገ-ወጥ የደን ሥራዎች ላይ በተደረገ ዘመቻ የማዕድን ቁፋሮ መሳሪያዎችን መያዟ ተዘገበ
በአካባቢ ጥበቃ ልዩ ሥፍራ በሚሰጠው የኒዩንግ ደቡብ ጥብቅ ደን ውስጥ የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል በሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ሰባት ኤክስካቫተሮችን እና 18 የውሃ ፓምፖችን መያዙን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህ ዘመቻ ለደኖች ውድመት እና ለወንዞች ብክነት ምክንያት የሆነውን "ጋላምሴይ" ወይም ሕገ-ወጥ አነስተኛ የማዕድን ቁፋሮዎችን ለመዋጋት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች አካል እንደሆነ ተዘግቧል።
የኒዩንግ ደቡብ ደን በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው የብዝሀ ሕይወት ሥፍራ የሚል ስያሜን ያገኘ ሲሆን ሕገ-ወጥ የማዕድን ቆፋሪዎች ከባለሥልጣናትና ከሕጋዊ የማዕድን ሥራ ፈቃድ ባለቤቶች ጋር የሚጋጩበት መነሻ ምክንያት ሆኗል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
መንግሥት በመደበኛ ፍተሻዎች እና መሳሪያዎችን በመያዝ የሕግ ማስከበር ሥራውን ቢያጠናክርም፤ የአካባቢ ውድመት ግን ቀጥሏል። ተሟጋቾች የደን ክምችቶችን ከማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ለመጠበቅ ጠንካራ ሕግ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X