ሞሮኮ ካለፈው ዓመት 16 በመቶ ከፍ የሚል በጀት ለ2026 የጤና እና ትምህርት ዘርፍ መደበች
18:37 20.10.2025 (የተሻሻለ: 18:44 20.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሞሮኮ ካለፈው ዓመት 16 በመቶ ከፍ የሚል በጀት ለ2026 የጤና እና ትምህርት ዘርፍ መደበች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሞሮኮ ካለፈው ዓመት 16 በመቶ ከፍ የሚል በጀት ለ2026 የጤና እና ትምህርት ዘርፍ መደበች
ለእነዚህ ዘርፎች የተመደበው 140 ቢሊዮን ድርሃም (15 ቢሊዮን ዶላር) የሞሮኮን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 10 በመቶ ይሆናል። ውሳኔው በንጉሥ መሐመድ ስድስተኛ ከተመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በኋላ ይፋ ሆኗል።
የንጉሣዊው ቤተ-መንግሥት የዘንድሮው የ4.8 በመቶ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ ለጭማሪው ምክንያት እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ውሳኔ በቅርቡ የተሻሉ የመንግሥት አገልግሎቶችን በመጠየቅ ከተካሄዱት የወጣቶች ተቃውሞ በኋላ የተላለፈ ነው።
ምክር ቤቱ ከ35 ዓመት በታች ለሆኑ እጩዎች የምርጫ ውድድር ማቅለያ ደንብ እና 75 በመቶ የምርጫ ዘመቻ ወጪን የሚሸፍን የገንዘብ ድጋፍን ጨምሮ የወጣቶችንና የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለሙ የምርጫ ማሻሻያዎችን በተናጠል አጽድቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X