በናይጄሪያ የብያፍራ ተገንጣይ መሪን በመደገፍ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀሰቀሱ

ሰብስክራይብ

በናይጄሪያ የብያፍራ ተገንጣይ መሪን በመደገፍ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀሰቀሱ

እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች፦

መነሻ

የብያፍራ ሕዝቦች ቡድን መሪ የሆኑት የእንግሊዝ እና ናይጄሪያ ጥምር ዜጋ ተሟጋቹ ናምዲ ካኑ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቁ ሰልፎች ሰኞ ዕለት በመላው ናይጄሪያ ተቀስቅሰዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ካኑ ከ2021 ጀምሮ ውድቅ ባደረጉት የአሸባሪነት እና ሀገር ክህደት ወንጀል ተከስሰው ታስረዋል።

ምን ተፈጠረ?

◻ በተሟጋች ኦሞዬሌ ሶዎሬ በሚመራው ‘ናምዲ ካኑ አሁኑኑ ይፈቱ’ ዘመቻ ስር የተደራጁ መሰባሰቦችን ለማስቆም የጸጥታ ኃይሎች በአቡጃ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሰው እስር መፈጸማቸው ተዘግቧል።

◻ ፖሊስ ዋና ዋና መንገዶችን ዘግቷል፤ ወታደሮች እና የሀገሪቱ የደህንነት ኃይሎች ደግሞ ቁልፍ መገናኛዎችና የፌዴራል ቦታዎች ላይ ተሰማርተዋል።

◻ በሌጎስ፣ እንደ ሌኪ እና ኦጆታ ባሉ ችግር ያለባቸው ቦታዎች ላይ ‘የኃይል ማሳያ’ ተካሂዷል የተባለ ሲሆን ፖሊስ ይህ እርምጃ ዓላማው አለመረጋጋትን ለመከላከል እና ‘የነዋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ’ እንደሆነ ገልጿል።

ባለሥልጣናት ምን አሉ?

◻ መንግሥት የተቃውሞ ሰልፎቹ ፍርድ ቤቶች ላይ ጫና ለማሳደር የተደረጉ ሕገ-ወጥ ሙከራዎች እንደሆኑ ይገልጻል።

◻ የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ባዮ ኦናኑጋ በአቡጃ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ‘የተመሳቀለ’ ሲሉ በመገለጽ፤ የካኑ ጠበቃ በሰልፉ በመቀላቀል የሕግ ሥነ-ምግባር ጥሰዋል ብለዋል።

◻ የፖሊስ ኃላፊዎች ሰልፎቹ ‘የሕዝብን ሰላም እስካላስተጓጎሉ ድረስ’ እንደሚፈቀዱ አጽንኦት ሰጥተዋል።

◻ የአናምብራ ገዥ ቻርለስ ሶሉዶ ተገንጣይነትን እንደማይደግፉ ገልጸው፤ “የኢግቦ ሰው ናይጄሪያን ይፈልጋል፤ ናይጄሪያም የኢግቦን ሰው ትፈልጋለች” በማለት ካኑ ከተፈቱ በኋላ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አውድ

◻ የካኑ የብያፍራ ሕዝቦች ቡድን የ1967–1970 ብያፍራ ጦርነት ቅሬታዎች በማስተጋባት ለደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ ነፃነትን ይሟገታል።

◻ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ባለሥልጣናት ከባድ እርምጃ ወስደዋል ሲሉ ይከሳሉ፤ የጸጥታ ኤጀንሲዎች ደግሞ የወሰዱት እርምጃ የሀገሪቱን መረጋጋት ለመጠበቅ እንደሆነ አጥብቀው ይናገራሉ።

አሁናዊ ሁኔታ

◻ በአቡጃ እና ሌጎስ ከባድ የጸጥታ ጥበቃ እንደቀጠለ ሲሆን ባለሥልጣናት ያልተፈቀዱ ስብሰባዎች የሕዝብን ሥርዓት እንደጣሱ ተደርገው እንደሚወሰዱ አስጠንቅቀዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

◻ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች፤ ከናምዲ ካኑ ጠበቆች አንዱ የሆኑት አሎይ ኤጂማኮር በመጨረሻው ቪዲዮ (ቀይ ሸሚዝ ለብሰው) ይታያሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0