በእኛ ምርት ከሁለት ዓመት በላይ የተነዱ መኪናዎች አሉ - ከከብት አጥንት የፍሬን እና ፍሪሲዮን ሸራ የሚያመርተው ወጣት
18:09 20.10.2025 (የተሻሻለ: 21:44 20.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በእኛ ምርት ከሁለት ዓመት በላይ የተነዱ መኪናዎች አሉ - ከከብት አጥንት የፍሬን እና ፍሪሲዮን ሸራ የሚያመርተው ወጣት
በሃይሉ ሰቦቃ "አስኬማ" ብሎ የሰየመውን ከከብት አጥንት፣ ከሴራሚክ ቁርጥራጮች እና ከሌሎች የተጣሉ ዕቃዎች የፍሬን እና ፍሪሲዮን ሸራ የሚያመርተውን ድርጅት የመሰረተው ከ3 ዓመት በፊት ነበር።
ከተጣሉ ዕቃዎች 1ሺ 400 አይነት የመኪና ፍሬን አካላትን በማምረት ላይ መሆኑን የሚናገረው ወጣቱ፤ ባሳለፍነው ዓመት ብቻ ከ30 ቶን በላይ የከብት ከአጥንት ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ማንሳቱን ይናገራል።
"እስካሁን ከ6ሺህ 400 በላይ መኪናዎች የእኛኝ ምርት ተጠቅመዋል። ጥሬ ዕቃዎችን በቀላሉ ስለምናገኝ እየጠየቅን ያለነው አንድ ሦስተኛ የገበያውን ዋጋ ብቻ ነው" ብሏል።
ከስፑኒክ አፍሪካ ጋር በነበረው ቆይታ ለወጣቶች የሥራ ዕድል እንደፈጠረ አጫውቶናል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X