በትግራይ ክልል የሕክምና አገልግሎት በግዜያዊ ስፍራዎች እንዲሰጥ ተወሰነ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበትግራይ ክልል የሕክምና አገልግሎት በግዜያዊ ስፍራዎች እንዲሰጥ ተወሰነ
በትግራይ ክልል የሕክምና አገልግሎት በግዜያዊ ስፍራዎች እንዲሰጥ ተወሰነ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.10.2025
ሰብስክራይብ

በትግራይ ክልል የሕክምና አገልግሎት በግዜያዊ ስፍራዎች እንዲሰጥ ተወሰነ

በሰሜኑ ጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማት ወደ አገልግሎት ባለመመለሳቸው የህክምና አሰጣጥን የአርሶ አደር ቤቶችን በመከራየት ለማስቀጠል መወሰኑን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የህክምና ተቋማቱን ወደ ነበሩበት ለመመለስ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንደሚያስፈልግ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አማኑኤል ኃይለ (ዶ/ር) ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ እና የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት፦

◻ በክልሉ የሚገኙ 89 በመቶ የሚሆኑት የጤና ተቋማት ጉዳት እንደደረሰባቸው፤ 3 በመቶ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን፣

◻ 99 በመቶ የህክምና ዕቃዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ፣ 72 በመቶ ከፍተኛ ጉዳት እንደሆነ እና 27 በመቶ የሚሆኑት መውደማቸውን አመላክቷል፡፡

ከ46ሺህ በላይ የኤችአይቪ ኤድስ ክትትል የሚያደርጉ ታካሚዎች ውስጥ 37ሺህ የሚሆኑት ተገኝተው ህክምናቸውን ሲቀጥሉ ቀሪዎቹ ያሉበት አይታወቅም ተብሏል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0