የናይጄሪያ ጦር በነዳጅ ስርቆት የተሠማሩ 28 ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል፤ አራት ሕገ-ወጥ የማጣሪያ ጣቢያዎችን ዘጋ
16:39 20.10.2025 (የተሻሻለ: 16:54 20.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያ ጦር በነዳጅ ስርቆት የተሠማሩ 28 ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል፤ አራት ሕገ-ወጥ የማጣሪያ ጣቢያዎችን ዘጋ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ ጦር በነዳጅ ስርቆት የተሠማሩ 28 ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል፤ አራት ሕገ-ወጥ የማጣሪያ ጣቢያዎችን ዘጋ
በነዳጅ የበለጸገው የናይጀር ዴልታ ክልል ውስጥ ባካሄደው የሁለት ሳምንት ሰፊ ዘመቻ፤ ከ290 ሺ ሊትር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኙ የነዳጅ ምርቶችን እንደወረሰ የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት አስታውቋል።
ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 9 በተካሄደው የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ የተሰረቀ ድፍድፍ ነዳጅ እና የተጣሩ ምርቶችን በማዘዋወር ላይ የተሳተፉ በርካታ መርከቦችንና የጭነት መኪናዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል ሲሉ የ6ኛው የጦር ሠራዊት ክፍል ተጠባባቂ የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል ዳንጁማ ዮናስ ዳንጁማ ገልፀዋል።
ወታደራዊ ባለሥልጣናት የሠራዊቱን ስኬት አሞካሽተው፤ በናይጄሪያ ደቡባዊ ክልሎች ከድፍድፍ ነዳጅ ስርቆት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን ለመዋጋት እየተደረገ ያለው ጥረት ጥብቅ ክትትል እንደሚያስፈልገው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያ ጦር በነዳጅ ስርቆት የተሠማሩ 28 ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል፤ አራት ሕገ-ወጥ የማጣሪያ ጣቢያዎችን ዘጋ

© telegram sputnik_ethiopia
/