ችግር የፈጠራ እናት ናት፦ የታካሚዎች መቆጣጠሪያ (ሞኒተር) የሠራው ኢትዮጵያዊ ዶክተር
16:11 20.10.2025 (የተሻሻለ: 16:24 20.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ችግር የፈጠራ እናት ናት፦ የታካሚዎች መቆጣጠሪያ (ሞኒተር) የሠራው ኢትዮጵያዊ ዶክተር
በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ኒራቅ የጤና ጣቢያ እየሠራ የሚገኘው ዶክተር ዮሐንስ ዘሪሁን፤ የህክምና መሳሪያ ጉድለት ለፈጠራው መነሻ እንደነበር ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ገልጿል፡፡ በመቆጣጠሪያ እጥረቱ ምክንያት ታካሚውን ያጣበትን አጋጣሚም አጋርቶናል፡፡
ሞኒተሩ በባትሪ እና በኤሌክትሪክ የሚሠራ ነው፡፡
“የምኖረው ከአዲስ አበባ 800 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኝ ከተማ ውስጥ ነው። በጦርነት እና በተፈጥሮ አደጋዎች በጣም የተጎዳ ነው፡፡ በከተማው በአግባቡ ኤሌክትሪክ አናገኝም። በዚህ ምክንያት የኃይል ምንጭ ለሞኒተሩ ችግር እንዳይሆን በኤሌክትሪክም ሆነ በባትሪ እንዲሠራ አድርጌዋለሁ፡፡
የተበላሹ የህክምና መሳሪያዎች እና የተጣሉ ብረቶችን በመጠቀም የተሠራው ሞኒተር አሁን ላይ በጤና ጣቢያው አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡
“ልዩ የሚያደርገው ዋጋው ርካሽ ነው። ተመጣጣኝ ነው፣ ለመጠገንም ቀላል ነው እንዲሁም ለጤና ጣቢያ የተመቸ ነው፡፡”
ዶክተር ዮሐንስ ሁለት ፈጠራዎችን፤ የኦፕሬሽን ክፍል ጠረጴዛ እና የአንጀት ካንሰር ታካሚዎች የሰገራ ማስወጫ መሳሪያ፤ ሠርቶ ለቅዱስ ፓውሎስ የህክምና ኮሌጅ አበርክቷል፡፡ እንዲሁም ከባለደረባው እና ከአስተማሪው ጋር በመሆን ሦስት ፈጠራዎችን እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጾልናል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/