የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለከፍተኛ ደረጃ ምክክር እና ቴክኖሎጂ ጉብኝት ወደ ሞስኮ አቀኑ
13:20 20.10.2025 (የተሻሻለ: 13:34 20.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለከፍተኛ ደረጃ ምክክር እና ቴክኖሎጂ ጉብኝት ወደ ሞስኮ አቀኑ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለከፍተኛ ደረጃ ምክክር እና ቴክኖሎጂ ጉብኝት ወደ ሞስኮ አቀኑ
ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ማክሰኞ እንደሚወያዩ ይጠበቃል ሲል በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንጭ ለስፑትኒክ ገልፀዋል።
ጉዞው ተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ ስብሰባዎችን እና በሩሲያ ዋና የፈጠራ ማዕከል ስኮልኮቮ ጉብኝትን ያካትታል ሲሉ ምንጩ አመልክተዋል።
ይህ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የቅርብ ግዜ የጠበቀ እና የከፍተኛ ደረጃ ግንኙነት የሚያስቀጥል ነው።
🟠 በመስከረም ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሞስኮ የዓለም አቶሚክ ሳምንት ፎረም ላይ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ተገናኝተው ለቀጣይ ስብሰባቸው አዲስ አበባ እንዲመጡ ጋብዘዋቸዋል። ሁለቱ ወገኖች ለኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የድርጊት መርሃ-ግብርም ተፈራርመዋል።
🟠 ባለፈው ዓመት የካቲት ወር የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ከኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው የፑቲንን ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርበዋል። በጉብኝቱ የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ተረጋግጧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X