በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢኮ ቱሪዝም ባቡር ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ
12:04 20.10.2025 (የተሻሻለ: 12:14 20.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢኮ ቱሪዝም ባቡር ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ
መሠረተ ልማቱ የሶፍዑመር ዋሻና ሎጅ ፕሮጀክቶችን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ እየተገነባ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ አሁን የመጀመሪያው ምዕራፍ 2 ኪ.ሜ ግንባታ እንደተጠናቀቀ የኢትየጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
የኢኮ ቱሪዝም ባቡሩ፦
◻ በኢትዮጵያውን የተሠራ ነው፣
◻ በውስጡ 50 ሰዎችን መያዝ ይችላል፣
◻ 10 ሰዎችን ለከፍታ የመልከዓምድር ዕይታ ማስተናገድ ይችላል፣
◻ ቀጣይ ምዕራፍ የባቡር መስመር ግንባታው በሂደት ላይ ነው፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ሥራው የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን፣ የኢንዱስትሪ መንደሮችን፣ የግብርና ምርቶችን ለማጓጓዝ የሚያስችል የባቡር ሀዲድ ዝርጋታን ያለ ውጭ ጥገኝነት ለመከወን አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/