ሩሲያ እና ዩክሬን አሁን ባለው የጦርነት ግንባር ግጭቱን ማቆም አለባቸው - ትራምፕ
10:39 20.10.2025 (የተሻሻለ: 10:44 20.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ዩክሬን አሁን ባለው የጦርነት ግንባር ግጭቱን ማቆም አለባቸው - ትራምፕ
“78 በመቶ የሚሆነው መሬት በሩሲያ ተይዟል ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፤ ”የግጭቱ ተዋናይ ወገኖች ሌሎች አስቻይ ስምምነቶችን ጦርነቱ ከቆመ በኋላ መደራደር ይችላሉ” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
ዩክሬን መላውን የዶንባስ ክልል ለሩሲያ እንድትሰጥ አለመወያየታቸውንም ትራምፕ ጠቁመዋል።
አንድ የእንግሊዝ ሚዲያ በውይይቱ የተሳተፉ ሰዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዕለት እንደዘገበው፤ አርብ በተደረገው ስብሰባ ትራምፕ ዘለንስኪ ሰፊ ግዛቶችን ለሞስኮ እንዲሰጡ ገፋፍተዋቸዋል።
“ውይይቱ በትራምፕ ‘ጦርነቱን አሁን ባለበት የድንበር መስመር ላይ በማቆም ስምምነት’ እንዲደረግ በመወሰን ተጠናቋል” ሲል አንድ ምንጭ ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡
በዩክሬን ያለው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ “በኪየቭ አገዛዝ የዘር ማጥፋት የተፈጸመባቸውን ሰዎች ለመጠበቅ” ያለመ ሲሆን የመጨረሻው ግብ ደግሞ ዶንባስን ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣት እና የሩሲያን ደህንነት የሚያረጋግጡ ሁኔታዎችን መፍጠር መሆኑን ሞስኮ ደጋግማ ገልፃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X