ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
20:33 19.10.2025 (የተሻሻለ: 21:34 19.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል።
“ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሁሌም እናስታውሰዋለን።” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሕልፈት ሕይወታቸው ተሰምቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X