ኔታንያሁ ጋዛ በሚገኙ የሐማስ ዒላማዎች ላይ 'ጠንካራ እርምጃ' እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኔታንያሁ ጋዛ በሚገኙ የሐማስ ዒላማዎች ላይ 'ጠንካራ እርምጃ' እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታወቀ
ኔታንያሁ ጋዛ በሚገኙ የሐማስ ዒላማዎች ላይ 'ጠንካራ እርምጃ' እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.10.2025
ሰብስክራይብ

ኔታንያሁ ጋዛ በሚገኙ የሐማስ ዒላማዎች ላይ 'ጠንካራ እርምጃ' እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታወቀ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያ ለእስራኤል ጦር የተሰጠው የፍልስጤሙ ንቅናቄ በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃቶችን ከፍቷል ከሚሉ ዘገባዎች በኋላ ነው ሲል ጽሕፈት ቤታቸው ጨምሮ አስታውቋል።

መግለጫው ሲያትት፣ "የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሐማስ መጣሱን ተከትሎ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከመከላከያ ሚኒስትሩ እና ከደህንነት ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ምክክር አድርገዋል፤ እንዲሁም በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ የአሸባሪው ዒላማዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ሰጥተዋል" ብሏል።

እንደ እስራኤል ሚዲያዎች፣ በዛሬው ዕለት አገሪቱ በመከላከያ ሠራዊቷ ላይ ተፈፅሟል ለተባለው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በምትገኘው ራፋህ ላይ የአየር ድብደባ ፈጽማለች። የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ሐማስ በእስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎች ይ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል ሲል ገልጿል።

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ሥራ ላይ የዋለው መስከረም 30 ቀን ነበር። ያለፈው ሰኞ የአሜሪካ፣ የግብፅ፣ የኳታር እና የቱርክ መሪዎች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አዋጅ መፈራረማቸው ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0