የግብፅ ፕሬዝዳንት የዓለምን 'መራጭነትና መንታዌ አሠራርን ኮንነው የተባበሩት መንግሥታት ማሻሻያን ጠይቀዋል
18:54 19.10.2025 (የተሻሻለ: 19:04 19.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየግብፅ ፕሬዝዳንት የዓለምን 'መራጭነትና መንታዌ አሠራርን ኮንነው የተባበሩት መንግሥታት ማሻሻያን ጠይቀዋል

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የግብፅ ፕሬዝዳንት የዓለምን 'መራጭነትና መንታዌ አሠራርን ኮንነው የተባበሩት መንግሥታት ማሻሻያን ጠይቀዋል
አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ የአስዋን የዘላቂ ሰላምና ልማት ጉባኤን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውሶችን "መፍታት ባለመቻሉ እና ብቃት በማጣቱ" ወቅሰዋል።
ኤል-ሲሲ አፍሪካ የከፉ ግጭቶች፣ የልማት ፈተናዎች እና የአየር ንብረት አደጋዎች ተጋርጠውባት፣ የእነዚህ ውድቀቶች ገፈት ቀማሽ ሆናለች ብለዋል፡፡
የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብደላቲ ይህን አቋም አስተጋብተዋል፤ አሁን ያለውን የዓለም እውነታ እና የደቡባዊ ዓለም ምኞቶችን በተሻለ ሁኔታ ለማንፀባረቅ የዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አካላትን ያካተተ ማሻሻያ እንዲደረግ አሳስበዋል።
"በተለዋዋጭ ዓለም፣ በእንቅስቃሴ ላይ ያለች አኅጉር" በሚል መሪ ቃል የተሰባሰበው ፎረሙ፣ የሱዳን ቀውስ ላይም ትኩረቱን አድርጓል፡፡ ግብፅ ሱዳናውያን-መር የፖለቲካ እልባት እና ዘላቂ የተኩስ አቁም አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X